La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዮሐንስ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከርሱ የሰማነው ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት፣ እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ጨለማም በርሱ ዘንድ ከቶ የለም፤ የሚል ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእርሱ የሰማነውና ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት ይህ ነው፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእርሱ የሰማነውና ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት “እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም” የሚል ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።

Ver Capítulo



1 ዮሐንስ 1:5
19 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለድ​ሆች ዳኝ​ነ​ትን ለች​ግ​ረ​ኞ​ችም ፍር​ድን እን​ዲ​ያ​ደ​ርግ ዐወ​ቅሁ።


አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ቸልም አት​በ​ለኝ። ቸል ብት​ለኝ ግን ወደ ጕድ​ጓድ እን​ደ​ሚ​ወ​ር​ዱት እሆ​ና​ለሁ።


ክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎች ይጠ​ፋ​ሉና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ግን እነ​ርሱ ምድ​ርን ይወ​ር​ሳሉ።


ቅን​ነት ከም​ድር በቀ​ለች፥ ጽድ​ቅም ከሰ​ማይ ተመ​ለ​ከተ።


አሁ​ንም የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን እን​መ​ላ​ለስ።


ፀሐይ በቀን የሚ​ያ​በ​ራ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ በሌ​ሊ​ትም ጨረቃ የሚ​ወ​ጣ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ ለአ​ን​ቺስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም ብር​ሃ​ንሽ፥ አም​ላ​ክ​ሽም ክብ​ርሽ ይሆ​ናል።


አይ​ሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በላኩ ጊዜ የዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት ይህ ነው።


ሕይ​ወት በእ​ርሱ ነበረ፥ ሕይ​ወ​ትም የሰው ብር​ሃን ነበረ፤


ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​በ​ራው እው​ነ​ተ​ኛው ብር​ሃ​ንስ ወደ ዓለም የመ​ጣው ነው።


ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ፤ የሚ​ከ​ተ​ለኝ የሕ​ይ​ወት ብር​ሃ​ንን ያገ​ኛል እንጂ በጨ​ለማ ውስጥ አይ​መ​ላ​ለ​ስም” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


በዓ​ለም ሳለሁ፤ የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ።”


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተማ​ርሁ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እር​ሱን ራሱን በያ​ዙ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ኅብ​ስ​ቱን አነሣ።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።


በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


ከመጀመሪያ የሰማችኋት መልእክት፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ የምትል ይህች ናትና፤


ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።


ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።