La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በኀ​ይል እንጂ በቃል አይ​ደ​ለ​ምና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት የወሬ ጕዳይ ሳይሆን የኀይል ጕዳይ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል አይደለምና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእግዚአብሔር መንግሥት የንግግር ጉዳይ ሳይሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል አይደለምና።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 4:20
8 Referencias Cruzadas  

ወን​ጌ​ልን ለማ​ስ​ተ​ማር አላ​ፍ​ር​ምና፤ አስ​ቀ​ድሞ አይ​ሁ​ዳ​ዊን፥ ደግ​ሞም አረ​ማ​ዊን፥ የሚ​ያ​ም​ኑ​በ​ትን ሁሉ የሚ​ያ​ድ​ና​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይሉ ነውና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ጽድ​ቅና ሰላም፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የሆነ ደስታ ነው እንጂ መብ​ልና መጠጥ አይ​ደ​ለ​ምና።


በኀ​ይ​ልና በተ​አ​ም​ራት፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይ​ልና ድንቅ ሥራን በመ​ሥ​ራ​ትም፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አው​ራ​ጃ​ዎች ጀምሬ እስከ እል​ዋ​ሪ​ቆን ድረስ እንደ አስ​ተ​ማ​ርሁ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስ​ንም ወን​ጌል ፈጽሞ እንደ ሰበ​ክሁ እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


ለእኛ ለዳ​ን​ነው ግን ከአ​ይ​ሁድ፥ ከአ​ረ​ሚም ብን​ሆን ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጥበብ ነው።


ቃሌም፥ ትም​ህ​ር​ቴም መን​ፈ​ስ​ንና ኀይ​ልን በመ​ግ​ለጥ ነበር እንጂ በሚ​ያ​ባ​ብል በጥ​በብ ቃል አል​ነ​በ​ረም።


እና​ን​ተን ለማ​ነጽ እንጂ፥ እና​ን​ተን ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ጠን ሥል​ጣን እጅግ የተ​መ​ካ​ሁት መመ​ካት ቢኖር አላ​ፍ​ርም።


ወንጌላችን በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።