1 ዜና መዋዕል 5:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአጋራውያንና ከኢጣርዮን ከናፋስዮንና ከናዳብዮን ጋር ተዋጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም በአጋራውያን፣ በኢጡር፣ በናፌስ፣ በናዳብ ላይ ዘመቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአጋራውያንና ከይጡር ከናፊሽና ከናዳብ ጋር ተዋጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም የሀጋራውያን ነገዶች በሆኑት በየጡር፥ በናፊሽና በኖዳብ ሕዝቦች ላይ አደጋ ለመጣል ዘመቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአጋራውያንና ከኢጡር ከናፌስና ከናዳብ ጋር ተዋጉ። |
በሳኦልም ዘመን ከስደተኞች ጋር ተዋጉ፥ እነርሱም በእጃቸው ተመትተው ወደቁ፤ በገለዓድ ምሥራቅ በኩል ባለው ሀገር ሁሉ በድንኳኖቻቸው ተቀመጡ።