Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 5:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥ ጽኑ​ዓን ጋሻና ሰይፍ የሚ​ይዙ፥ ቀስ​ተ​ኞ​ችም፥ ሰልፍ የሚ​ያ​ውቁ ሰል​ፈ​ኞ​ችም፥ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የሮቤል፣ የጋድና የምናሴ ነገድ እኩሌታ አርባ አራት ሺሕ ሰባት መቶ ስድሳ ብቁ የጦር ሰዎች ነበሯቸው። እነርሱም ጋሻ መያዝ፣ ሰይፍ መምዘዝና ቀስት መሳብ የሚችሉ ጠንካራና በውጊያ የሠለጠኑ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የሮቤልና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ፥ ጽኑዓን፥ ጋሻና ሰይፍ የሚይዙ፥ ቀስተኞችም፥ የውግያ ስልት የሚያውቁ ተዋጊዎችም፥ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የሮቤል፥ የጋድና በስተ ምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ በጋሻና በሰይፍ እንዲሁም በቀስት ውጊያ በደንብ የሠለጠኑ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሥልሳ ወታደሮች ነበሩአቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የሮቤልና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኵሌታ፥ ጽኑዓን፥ ጋሻና ሰይፍ የሚይዙ፥ ቀስተኞችም፥ ሰልፍ የሚያውቁ ሰልፈኞችም፥ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 5:18
5 Referencias Cruzadas  

በሳ​ኦ​ልም ዘመን ከስ​ደ​ተ​ኞች ጋር ተዋጉ፥ እነ​ር​ሱም በእ​ጃ​ቸው ተመ​ት​ተው ወደቁ፤ በገ​ለ​ዓድ ምሥ​ራቅ በኩል ባለው ሀገር ሁሉ በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።


ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡ​ትን ሁሉ፥ አን​ተና አሮን በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ቍጠ​ሩ​አ​ቸው።


ሙሴም ለጋድ ልጆ​ችና ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለዮ​ሴ​ፍም ልጅ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን መን​ግ​ሥት፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን መን​ግ​ሥት፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም፥ ከተ​ራ​ሮ​ችም ጋር ከተ​ሞ​ችን፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ​ትን የም​ድ​ሪ​ቱን ከተ​ሞች ሰጣ​ቸው።


ኢያ​ሱም ሮቤ​ል​ንና ጋድን የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos