1 ዜና መዋዕል 26:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምሥራቁም በር ዕጣ ለሰሌምያና ለዘካርያ ወደቀ። የዮአስም ልጆች ለምልክያ ዕጣ ጣሉ፤ ዕጣውም በሰሜን በኩል ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምሥራቁ በር ዕጣ ለሴሌምያ ወጣ። ከዚያም ምክር ዐዋቂ ለሆነው ለልጁ ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ እርሱም የሰሜኑ በር ደረሰው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰሌምያም በምሥራቅም በኩል ዕጣ ወጣለት። ለልጁም ብልህ አማካሪ ለሆነው ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ የእርሱም ዕጣ በሰሜን በኩል ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሼሌምያ በምሥራቅ በኩል የሚገኘውን ቅጽር በር ለመጠበቅ ዕጣ ወጣለት፤ ዘወትር መልካም ምክር ይሰጥ የነበረው ልጁ ዘካርያስ ደግሞ በሰሜን በኩል የሚገኘውን ቅጽር በር ለመጠበቅ ዕጣ ወጣለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምሥራቅም በኩል ዕጣ ለሰሌምያ ወደቀ። ለልጁም ብልህ መካር ለሆነው ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ ዕጣውም በሰሜን በኩል ወጣ። |
የሌዋዊውም የይምላእ ልጅ የምሥራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያካፍል ሕዝቡ በፈቃዳቸው ለእግዚአብሔር በአቀረቡት ላይ ተሾመ።
ወደ አለቆቹም ወደ አልዓዛር፥ ወደ አርኤል፥ ወደ ሰማአያ፥ ወደ ሀሎናም፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ሄልናታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካርያስ፥ ወደ ሜሱላም፥ ደግሞም ወደ ዐዋቂዎቹ ወደ ዮያሪብና ወደ ሄልናታን ላክሁ።