መዝሙር 81:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቤ ሆይ፤ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ፤ እስራኤል ሆይ፤ ምነው ብታደምጠኝ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ አዳንሁህም፥ ከተሰወረ የሞገድ ስፍራ መለስሁልህ፥ በክርክር ውኃ ዘንድም ፈተንሁህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ ሆይ! የማስጠንቀቂያ ንግግሬን ስማ! እስራኤል ሆይ! ብታዳምጡኝ ምንኛ መልካም ነበር! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍረድ፥ አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና። |
እርሱም አለ፤ “የአምላካችሁን እግዚአብሔር ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፣ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብትፈጽሙ፣ ትእዛዞቹን ልብ ብትሉና ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቁ፣ በግብጻውያን ላይ ያመጣሁባቸውን ማንኛውንም ዐይነት በሽታ በእናንተ ላይ አላመጣም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
ስፍራውንም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፤ እስራኤላውያን ጠብ ፈጥረው፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ወይስ አይደለም” በማለት እግዚአብሔርን ተፈታትነዋልና።
በሦስተኛውም ቀን ጧት ከባድ ደመና በተራራው ላይ ሆኖ ነጐድጓድና መብረቅ እንዲሁም ታላቅ የቀንደ መለከት ድምፅ ነበር፤ በሰፈሩ ያሉት ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
እንዲህ አላቸው፤ “የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዝዟቸው፣ እኔ ዛሬ በግልጽ የምነግራችሁን ቃሎች ሁሉ በልባችሁ አኑሩ።
አንተ ቅረብ፤ አምላካችን እግዚአብሔር የሚለውን ሁሉ ስሙ፤ ከዚያም አምላካችን እግዚአብሔር የሚነግርህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንሰማለን፤ እናደርገዋለንም።”