መዝሙር 80:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ እንግዲህ ወደ እኛ ተመለስ፤ ከሰማይ ተመልከት፤ እይም፤ ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዱር እርያ አረከሳት፥ የአገር አውሬም ተሰማራባት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ ሆይ! ፊትህን ወደ እኛ መልስ! ከሰማይ ወደ እኛ ወደ ታች ተመልከት፤ እይም፤ ይህን የወይን ግንድህን ጠብቅ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥ በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፤ |
ከተቀደሰው፣ ከተከበረውና ከፍ ካለው ዙፋንህ፣ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ኀይልህና ቅናትህ የት አለ? ገርነትህና ርኅራኄህ ከእኛ ርቀዋል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከመንገድህ እንድንወጣ፣ ልባችንን በማደንደን ለምን እንዳንፈራህ አደረግኸን? ስለ ባሮችህ ስትል፣ ስለ ርስትህ ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።
በምሕረቱ ተመልሶ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን እንዲተርፋችሁ፣ በረከቱን ይሰጣችሁ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?
ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ብላችኋል፤ አልጠበቃችኋቸውምም፤ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። “እናንተ ግን፣ ‘የምንመለሰው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ።