ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ “በእግዚአብሔር ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ይባላል።
መዝሙር 46:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን፣ በሚደርስብን መከራ ሁሉ የቅርብ ረዳታችን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ምሥጢር፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤ ችግር በሚደርስብን ጊዜ ሁሉ ረዳታችን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለአግዚአብሔር እልል በሉ። |
ከዚህም የተነሣ አብርሃም የዚያን ስፍራ ስም፣ “እግዚአብሔር ያዘጋጃል” ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ፣ “በእግዚአብሔር ተራራ ላይ ይዘጋጃል” ይባላል።
“ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ነቢያትን የምትገድዪ፣ ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ፣ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈቀዳችሁም፤
እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል።