መዝሙር 4:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስትቈጡ ኀጢአት አትሥሩ፤ በዐልጋችሁም ላይ ሳላችሁ፣ ልባችሁን መርምሩ፤ ጸጥም በሉ። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፥ ጌታ ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ያኽል ብትበሳጩ ኃጢአት አትሥሩ፤ በምትተኙበት ስፍራ በጸጥታ ልባችሁን መርምሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተቈጡ፥ ነገር ግን አትበድሉ፤ በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ የምታስቡት ይታወቃችሁ። |
ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን? ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣ አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤ ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤ ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።
በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?