መዝሙር 16:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤ በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመከረኝን አምላክ እባርካለሁ፥ ደግሞም በሌሊት ኩላሊቶቼ ይገሥጹኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚመክረኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሌሊት እንኳ ሕሊናዬ ያስተምረኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀኝህን ከሚቃወሟት፥ የሚያምኑብህን የሚያድናቸውን ቸርነትህን ግለጠው። |
የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ።
ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤ በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።
ልጆቿንም በሞት እቀጣቸዋለሁ። ከዚያም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እኔ ልብንና ሐሳብን የምመረምር መሆኔን ይረዳሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እከፍላችኋለሁ።