መዝሙር 143:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቼንም ለእኔ ስላለህ ምሕረት ደምስሳቸው፤ እኔ ባሪያህ ነኝና፣ ነፍሴን የሚያስጨንቋትን ሁሉ አጥፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽኑ ፍቅርህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባርያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ግለጥልኝ፤ ጠላቶቼን አጥፋቸው፤ እኔ አገልጋይህ ስለ ሆንኩ ጥቃት የሚያደርሱብኝን ሁሉ ደምስሳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቻቸው በጐልማስነታቸው እንደ አዲስ ተክል የሆኑ፥ ሴቶች ልጆቻቸውም እንደ እልፍኝ ያማሩና ያጌጡ፤ |
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፣ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፣ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል።