ታምራታዊ ምልክቶችንና ድንቆችን በፈርዖንና፣ በሹማምቱ ሁሉ፣ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ላክህ፤ ይህንም ያደረግኸው ግብጻውያን እንዴት በእብሪት እንዳስጨነቋቸው ስላወቅህ ነው። እስከ ዛሬም የሚጠራ ስም ለራስህ እንዲኖርህ አደረግህ።
መዝሙር 135:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግብጽ ሆይ፤ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣ በመካከልሽ ታምራትንና ድንቅን ሰደደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግብጽ ሆይ፥ በመካከልሽ በፈርዖንና በባርያዎቹ ሁሉ ላይ ተኣምራትንና ድንቅን ሰደደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ ንጉሡን ፈርዖንንና አገልጋዮቹን ሁሉ ለመቅጣት ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጨረቃና ለከዋክብት ሌሊትን ያስገዛቸው፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ |
ታምራታዊ ምልክቶችንና ድንቆችን በፈርዖንና፣ በሹማምቱ ሁሉ፣ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ላክህ፤ ይህንም ያደረግኸው ግብጻውያን እንዴት በእብሪት እንዳስጨነቋቸው ስላወቅህ ነው። እስከ ዛሬም የሚጠራ ስም ለራስህ እንዲኖርህ አደረግህ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር በዐይናችሁ እያያችሁ ለእናንተ በግብጽ እንዳደረገው ሁሉ በፈተና፣ በታምራዊ ምልክቶችና በድንቆች፣ በጦርነት፣ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ወይም በታላቅና በአስፈሪ ሥራዎች ከሌላ ሕዝብ መካከል አንድን ሕዝብ የራሱ ለማድረግ የቻለ አምላክ አለን?
እኛ በዐይናችን እያየን እግዚአብሔር ታላላቅና አስፈሪ የሆኑ ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆችን በግብጽ፣ በፈርዖንና በመላው ቤተ ሰዎቹ ላይ አደረገ።