ለራሳችሁ፣ በመካከላችሁ ለሚኖሩት ልጆች ላሏቸው መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ መድቡ፤ እነርሱንም እንደ እስራኤል ተወላጆች ቍጠሯቸው፤ እንደ እናንተ ከእስራኤል ነገዶች ርስት ይመደብላቸው።
ዘኍል 26:56 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱም ርስት በትልልቆቹና በትንንሾቹ ነገዶች መካከል በዕጣ ይደለደላል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብዙዎችና በጥቂቶች መካከል ርስታቸው በዕጣ ትከፋፈላለች።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕጣ የሚጣለውም ከፍተኛ ቊጥርና አነስተኛ ቊጥር ባላቸው ቤተሰቦች መካከል ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብዙዎችና በጥቂቶች መካከል ርስታቸውን በዕጣ ትከፍላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብዙዎችና በጥቂቶች መካከል ርስታቸው በዕጣ ትከፈላለች። |
ለራሳችሁ፣ በመካከላችሁ ለሚኖሩት ልጆች ላሏቸው መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ መድቡ፤ እነርሱንም እንደ እስራኤል ተወላጆች ቍጠሯቸው፤ እንደ እናንተ ከእስራኤል ነገዶች ርስት ይመደብላቸው።
በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ በጌርሶን በኩል፣ የጌርሶናውያን ጐሣ፣ በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጐሣ፣ በሜራሪ በኩል፣ የሜራራውያን ጐሣ፤