ዘኍል 26:54 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርከት ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቍጥር መሠረት ይረከባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው ለብዙዎቹ እንደ ብዛታቸው፥ ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣቸዋለህ። ለሁሉ እንደ ቁጥራቸው መጠን ርስታቸው ይሰጣቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዛት ላለው ነገድ ሰፊ መሬት፥ አነስተኛ ቊጥር ለሆነ ነገድ ጠበብ ያለ መሬት ስጥ፤ የርስቱም ክፍፍል በቈጠራ በተገኘው የሕዝብ ብዛት መሠረት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለብዙዎቹ ብዙ ርስትን ትሰጣቸዋለህ፤ ለጥቂቶችም ጥቂት ርስትን ትሰጣቸዋለህ። ለእያንዳንዳቸው እንደ ቍጥራቸው መጠን ርስታቸውን ትሰጣቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለብዙዎቹ እንደ ብዛታቸው፥ ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣቸዋለህ። ለሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን ርስታቸው ይሰጣቸዋል። |
ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቍጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቍጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን።
እስራኤላውያን ከወረሷት ምድር ላይ ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው ከተሞች እያንዳንዱ ነገድ እንዳለው ድርሻ መጠን ይሆናል። ብዙ ካለው ነገድ ላይ ብዙ ከተሞች እንዲሁም ጥቂት ካለው ነገድ ላይ ጥቂት ከተሞችን ውሰዱ።”
የዮሴፍ ዘሮች ኢያሱን፣ “ቍጥራችን ብዙ ነው፤ እግዚአብሔርም አብዝቶ ባርኮናል፤ ታዲያ እንዴት ርስታችን አንድ ዕጣና አንድ ድርሻ ብቻ ሆነ?” አሉት።
የይሁዳ ነገድ የያዘው ርስት እጅግ ሰፊ ስለ ነበር፣ ከይሁዳ ነገድ ድርሻ ተከፍሎ ለስምዖን ነገድ በርስትነት ተሰጠ። ከዚህ የተነሣም የስምዖን ነገድ በይሁዳ ነገድ ድርሻ ርስት ሊካፈል ቻለ።