ዘኍል 14:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? እነዚህን ሁሉ ታምራት በመካከሉ እያደረግሁ የማያምንብኝስ እስከ መቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? በመካከላቸውም ስላደረግሁት ተአምራት ሁሉ እንኳ እስከ መቼ ድረስ በእኔ አያምኑም? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ እኔን የሚንቀው እስከ መቼ ነው? ብዙ ተአምራትን በፊቱ አድርጌአለሁ፤ ታዲያ፥ በእኔ መታመንን እምቢ የሚለው እስከ መቼ ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እኒህ ሕዝብ እስከ መቼ ያስቈጡኛል? በፊታቸውስ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ እስከ መቼ አያምኑብኝም? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? በፊቱስ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ እስከ መቼ አያምንብኝም? |
ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ አሉት፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ራስህን በፊቴ ለማዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ሕዝቤ ያመልኩኝ ዘንድ ልቀቃቸው።
“እናንተ አላዋቂዎች፤ ማስተዋል የሌለበት መንገዳችሁን እስከ መቼ ትወድዱታላችሁ? ፌዘኞች በፌዝ ደስ የሚሰኙት፣ ሞኞችስ ዕውቀትን የሚጠሉት እስከ መቼ ነው?
ቃሌን መስማት እንቢ ብለው በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ ሊያመልኳቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን ጣዖቶች የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝቦች ከጥቅም ውጭ እንደ ሆነው እንደዚህ መቀነት ይበላሻሉ።
“ ‘ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ ዐመፀብኝ፤ ሰው ቢጠብቀው በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዐቴን አልጠበቁም፤ ሕጌንም ተላለፉ፤ ሰንበቴንም ፈጽሞ አረከሱ። እኔም መዓቴን ላፈስስባቸው፣ በምድረ በዳም ላጠፋቸው ወስኜ ነበር።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ባስቈጡኝ ጊዜ ያለ አንዳች ሐዘኔታ ጥፋት ላመጣባችሁ እንደ ወሰንሁ፣” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት፤
ኢየሱስም፣ “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጁን ወደዚህ አምጡት!” አለ።
ኢየሱስም መልሶ፣ “የማታምን ትውልድ ሆይ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጁን ወደ እኔ አምጡት።” አላቸው።
ሌላ ሰው ያላደረገውን በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ፣ ኀጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን እነዚህን ታምራት አይተዋል፤ ሆኖም እኔንም አባቴንም ጠልተዋል።