‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤ አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ!’ የሚሉ ናቸው። እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።
ማርቆስ 2:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈሪሳውያን ጸሐፍት ከኀጢአተኞችና ከቀረጥ ሰብሳቢዎች ጋራ ሲበላ ባዩት ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱን “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኀጢአተኞች ጋራ ለምን ይበላል?” ሲሉ ጠየቋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጸሐፍት ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድነው?” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ የሕግ መምህራን ኢየሱስ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው “ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላውና የሚጠጣው ስለምንድን ነው?” በማለት ደቀ መዛሙርቱን ጠየቁአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራ ጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ፦ ከቀራ ጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው? አሉ። |
‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤ አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ!’ የሚሉ ናቸው። እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።
በሌዊም ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ፣ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ኀጢአተኞች ተከትለውት ስለ ነበር፣ ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ዐብረው ይመገቡ ነበር።
“ይህ ሰው እንዴት እንዲህ ይላል? በአምላክ ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ እኮ ነው! ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው አሰቡ።
ፈሪሳዊውም ቆሞ ስለ ራሱ እንዲህ ይጸልይ ነበር፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ እንደ ሌላው ሰው ሁሉ ቀማኛ፣ ዐመፀኛ፣ አመንዝራ፣ ይልቁንም እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ባለመሆኔ አመሰግንሃለሁ፤
ፈሪሳውያንና ጸሐፍታቸውም “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ‘ከኀጢአተኞች’ ጋራ የምትበሉትና የምትጠጡት ለምንድን ነው?” እያሉ በደቀ መዛሙርቱ ላይ አጕረመረሙ።
ታላቅ ሁከትም ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ የኦሪት ሕግ መምህራንም ተነሥተው፣ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮትስ እንደ ሆነ ምን ይታወቃል?” በማለት አጥብቀው ተከራከሩ።