ሰቈቃወ 1:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ፤ በዓላቷን ለማክበር የሚመጣ የለምና፤ በበሮቿ ሁሉ የሚገባና የሚወጣ የለም፤ ካህናቷ ይቃትታሉ፤ ደናግሏ ክፉኛ ዐዝነዋል፤ እርሷም በምሬት ትሠቃያለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ድንግሎችዋም ተጨነቁ እርሷም በምሬት አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው በዓላቱን ለማክበር ስለማይመጣ የጽዮን መንገዶች ጭር ይላሉ፤ በሮችዋ ሁሉ ባዶ ናቸው፤ ካህናትዋ ይቃትታሉ ልጃገረዶችዋ በሐዘን ይጨነቃሉ የጽዮንም ዕድል ፈንታ የመረረ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፤ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል፤ ካህናቷም ያለቅሳሉ፤ ደናግሎችዋም ተማረኩ፤ እርስዋም በምሬት አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ደናግሎችዋም ተጨነቁ እርስዋም በምሬት አለች። |
“ሰዎች የሥቃይ ልቅሶዬን ሰሙ፤ የሚያጽናናኝ ግን ማንም የለም፤ ጠላቶቼ ሁሉ ጭንቀቴን ሰሙ፤ አንተ ባደረግኸውም ደስ አላቸው፤ አቤቱ የተናገርሃት ቀን ትምጣ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሁኑ።
ለበኣል አማልክት ዕጣን ስላጠነችባቸው ቀናት እቀጣታለሁ፤ በጌጣጌጥና በቀለበቶች ራሷን አስጊጣለች፤ ውሽሞቿንም ተከትላ ሄዳለች፤ እኔን ግን ረስታለች” ይላል እግዚአብሔር።
የዱር አራዊትን እሰድድባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁን ይነጥቋችኋል፤ ከብቶቻችሁን ያጠፉባችኋል፤ ቍጥራችሁ ይመነምናል፤ መንገዶቻችሁም ሰው አልባ ይሆናሉ።
ስለዚህ በእናንተ ምክንያት፣ ጽዮን እንደ ዕርሻ ትታረሳለች፣ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ የቤተ መቅደሱም ኰረብታ ዳዋ የወረሰው ጕብታ ይሆናል።