ኤርምያስ 51:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ባዕዳን ሰዎች ወደ ተቀደሰው፣ ወደ እግዚአብሔር ቤት ስለ ገቡ፣ እኛ ተሰድበናል፤ ዕፍረትም ፊታችንን ሸፍኗል፤ ውርደትም ተከናንበናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም በጌታ ቤት ውስጥ ወዳሉት ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ገብተዋልና ውርደት ፊታችንን ሸፍኖታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ስለ ተሰደብን አፈርን፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ባዕዳን ሰዎች ስለ ገቡ ተዋርደን አንገታችንን ደፋን።’ በሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድባችንን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም ወደ ቤተ መቅደሳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብተዋልና ውርደት ፊታችንን ከድኖታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፥ ባዕዳን ሰዎችም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብተዋልና ነውር ፊታችንን ከድኖታል። |
እግዚአብሔር ለያዕቆብ ይራራለታል፤ እስራኤልን እንደ ገና ይመርጠዋል፤ በራሳቸውም አገር ያኖራቸዋል። መጻተኞች ዐብረዋቸው ይኖራሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋራ ይተባበራሉ።
በባሕሩ ዳር ባለው ምድረ በዳ ላይ የተነገረ ንግር፤ ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እየጠራረገ እንደሚመጣ፣ ወራሪ ከአሸባሪ ምድር፣ ከምድረ በዳ ይመጣል።
“አንቺ የባቢሎን ድንግል ልጅ ሆይ፤ ውረጂ፤ በትቢያ ላይ ተቀመጪ፤ አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ከዙፋንሽ ውረጂ፤ መሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ውብ ወይም ለግላጋ፣ ተብለሽ አትጠሪም።
መሳፍንት አገልጋዮቻቸውን ውሃ ፍለጋ ይሰዳሉ፤ እነርሱ ወደ ውሃ ጕድጓዶች ይወርዳሉ፤ ነገር ግን ውሃ አያገኙም፤ ዐፍረውና ተስፋ ቈርጠው፣ ራሳቸውን ተከናንበው፣ ባዶ እንስራ ይዘው ይመለሳሉ።
በቅርብና በሩቅ ያሉትን የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ በማከታተል፣ በምድር ላይ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ አጠጣኋቸው፤ ከእነዚህም ሁሉ በኋላ የሼሻክ ንጉሥ ደግሞ ይጠጣል።
የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ፣ ቤተ መንግሥቱን እንዲሁም በኢየሩሳሌም የሚገኙትን ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤ እያንዳንዱንም ትልልቅ ሕንጻዎችንም በእሳት አወደመ።
“አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እይ፤ ተመልከትም፤ በማን ላይ እንዲህ አድርገህ ታውቃለህ? በውኑ እናቶች ሕፃኖቻቸውን፣ ተንከባክበው ያሳደጓቸውን ልጆች ይብሉን? ካህኑና ነቢዩስ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ይገደሉን?
ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የኀይላችሁን ትምክሕት፣ የዐይናችሁ ማረፊያና የልባችሁ ደስታ የሆነውን መቅደሴን አረክሳለሁ። ትታችኋቸው የሄዳችሁ ወንድና ሴት ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
እርሱም፣ “ቤተ መቅደሴን አርክሱ፤ አደባባዩንም ሬሳ በሬሳ አድርጉ፤ ሂዱ!” አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማዪቱ ሁሉ እየተዘዋወሩ መግደል ጀመሩ።
“የጦር ሰራዊቱም ቤተ መቅደሱንና ቅጥሩን ያረክሳሉ፤ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፤ በዚያም ጥፋትን የሚያመጣውን የጥፋት ርኩሰት ይተክላሉ።
የዖምሪን ሥርዐት፣ የአክዓብን ቤት ልምድ ሁሉ የሙጥኝ ብለሃል፤ ትውፊታቸውንም ተከትለሃል። ስለዚህ አንተን ለውድመት፣ ሕዝብህን ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ አሕዛብም ይሣለቁብሃል።”
ጠላቴም ታያለች፤ ኀፍረትንም ትከናነባለች፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ያለችኝን፣ ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤ አሁንም እንኳ፣ እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።