ዳዊት ግን እያለቀሰ የደብረ ዘይትን ተራራ ሽቅብ ወጣ፤ ራሱን ተከናንቦ፣ ባዶ እግሩን ነበር፤ ዐብሮት ያለውም ሕዝብ ሁሉ እንደዚሁ ራሱን ተከናንቦ እያለቀሰ ሽቅብ ይወጣ ነበር።
ኤርምያስ 14:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሳፍንት አገልጋዮቻቸውን ውሃ ፍለጋ ይሰዳሉ፤ እነርሱ ወደ ውሃ ጕድጓዶች ይወርዳሉ፤ ነገር ግን ውሃ አያገኙም፤ ዐፍረውና ተስፋ ቈርጠው፣ ራሳቸውን ተከናንበው፣ ባዶ እንስራ ይዘው ይመለሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላላቆቻቸውም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ላኩ፤ ወደ ጉድጓድ መጡ ውኃም አላገኙም፥ ዕቃቸውንም ባዶውን ይዘው ተመለሱ፤ አፈሩም ተዋረዱም ራሳቸውንም ተከናነቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብታሞች ውሃ ለማግኘት ሠራተኞቻቸውን ይልካሉ፤ እነርሱም ወደ ውሃ ጒድጓዶች ይሄዳሉ፤ ነገር ግን ምንም ውሃ ስለማያገኙ፥ ባዶ እንስራ ተሸክመው ይመለሳሉ፤ ተስፋ ቈርጠው ግራ ስለሚጋቡ፥ በሐዘን ራሳቸውን ይሸፍናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላላቆችዋም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ሰደዱ፤ ወደ ጕድጓድ መጡ፤ ውኃም አላገኙም፤ ዕቃቸውንም ባዶውን መለሱ፤ ዐፈሩም፤ ተዋረዱም፤ ራሳቸውንም ተከናነቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላላቆችም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ሰደዱ፥ ወደ ጕድጓድ መጡ ውኃም አላገኙም፥ ዕቃቸውንም ባዶውን ይዘው ተመለሱ፥ አፈሩም ተዋረዱም ራሳቸውንም ተከናነቡ። |
ዳዊት ግን እያለቀሰ የደብረ ዘይትን ተራራ ሽቅብ ወጣ፤ ራሱን ተከናንቦ፣ ባዶ እግሩን ነበር፤ ዐብሮት ያለውም ሕዝብ ሁሉ እንደዚሁ ራሱን ተከናንቦ እያለቀሰ ሽቅብ ይወጣ ነበር።
“ሕዝቅያስን አትስሙ። የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፤ ‘ከእኔ ጋራ ተስማሙ፤ ወደ እኔም ውጡ። ከዚያም እያንዳንዳችሁ ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤
“ሕዝቤ ሁለት ኀጢአት ፈጽመዋል፤ ሕያው የውሃ ምንጭ የሆንሁትን፣ እኔን ትተዋል፤ ውሃ መያዝ የማይችሉትን ቀዳዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓዶች፣ ለራሳቸው ቈፍረዋል።
ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋራ ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም።
አለዚያ ገፍፌ ዕርቃኗን አስቀራታለሁ፤ እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፤ እንደ ምድረ በዳ፣ እንደ ደረቅም ምድር አደርጋታለሁ፤ በውሃ ጥምም እገድላታለሁ።
“መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ ዝናብ ከለከልኋችሁ፤ በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤ በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ ሌላው ዝናብ ዐጥቶ ደረቀ።