ነገር ግን ውሃው የምድርን ገጽ ገና እንደ ሸፈነ ስለ ነበር፣ ተመልሳ ኖኅ ወዳለበት መርከብ መጣች፤ እርሱም እጁን ዘርግቶ ተቀበላት፤ ወደ መርከቢቱም አስገባት።
2 ቆሮንቶስ 7:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ መቄዶንያ በመጣን ጊዜ፣ ከየአቅጣጫው መከራ ደረሰብን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አላገኘም፤ ከውጭ ጠብ፣ ከውስጥ ደግሞ ፍርሀት ነበረብን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አልነበረውም፤ ከውጭ ጠብ ነበረ፤ ከውስጥ ደግሞ ፍርሃት ነበረብን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቄዶንያ በደረስን ጊዜ እንኳ ከብዙ አቅጣጫ ችግር ደረሰብን እንጂ ምንም ዕረፍት አላገኘንም፤ በውጭ ጠብ በውስጥም ፍርሀት ነበረብን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ መቄዶንያም በደረስን ጊዜ ለሰውነታችን ጥቂት ስንኳን ዕረፍት አላገኘንም፤ በሁሉም መከራ አጸኑብን እንጂ፤ በውጭም መጋደል ነበር፤ በውስጥም ፍርሀት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሥጋችን ዕረፍት አልነበረውም፤ በውጭ ጠብ ነበረ፥ በውስጥ ፍርሃት ነበረ። |
ነገር ግን ውሃው የምድርን ገጽ ገና እንደ ሸፈነ ስለ ነበር፣ ተመልሳ ኖኅ ወዳለበት መርከብ መጣች፤ እርሱም እጁን ዘርግቶ ተቀበላት፤ ወደ መርከቢቱም አስገባት።
“በየቦታው ሽብር አለ፤ አውግዙት፤ እናውግዘው፤” ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤ መውደቄን በመጠባበቅ፣ ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣ “ይታለል ይሆናል፣ ከዚያም እናሸንፈዋለን፤ እንበቀለዋለንም” ይላሉ።
ባለፈው ጊዜ እንደዚያ የጻፍሁላችሁ ወደ እናንተ ስመጣ ደስ ሊያሠኙኝ የሚገባቸው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ በማለት ነው፤ ምክንያቱም የእኔ ደስታ የሁላችሁ ደስታ እንደሚሆን አምናለሁ።
ስለዚህ ምንም መታገሥ ባልቻልሁ ጊዜ ስለ እምነታችሁ ለማወቅ ላክሁ፤ ይህንም ያደረግሁት ምናልባት ፈታኙ ፈትኗችሁ ድካማችን ሁሉ ከንቱ ሆኗል ብዬ ስለ ፈራሁ ነው።