La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 14:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በምርኮው ላይ ተረባርበው በጉን፣ በሬውንና ጥጃውን በመውሰድ በመሬት ላይ ዐርደው ሥጋውን ከነደሙ በሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በምርኮው ላይ ተረባርበው በጉን፥ በሬውንና ጥጃውን በመውሰድ በመሬት ላይ ዐርደው ሥጋውን ከነደሙ በሉት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ከጠላት ባገኙት ምርኮ ላይ እየተረባረቡ በጎችን፥ የቀንድ ከብቶችንና ጥጆችን ባገኙበት ቦታ እያረዱ ሥጋውን ከነደሙ መብላት ጀመሩ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝ​ቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎ​ችን፥ በሬ​ዎ​ች​ንም፥ ጥጆ​ች​ንም ወስ​ደው እን​ዳ​ገኙ በም​ድር ላይ አረዱ፤ ሕዝ​ቡም ከደሙ ጋር በሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሕዝቡም ለምርኮ ሳሱ፥ በጎችን በሬዎችንም ጥጆችንም ወስደው በምድር ላይ አረዱ፥ ሕዝቡም ከደሙ ጋር በሉ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 14:32
11 Referencias Cruzadas  

“ነገር ግን ሕይወቱ፣ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።


ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ዐይኖቻችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምም ታፈስሳላችሁ፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን ልትወርሱ ታስባላችሁ?


“ ‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ሥጋ አትብሉ። “ ‘ጥንቈላ ወይም አስማት አትሥሩ።


“ ‘በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ፣ ሥብ ወይም ደም ከቶ አትብሉ፤ ይህ ለመጪው ትውልድ ሁሉ የተሰጠ የዘላለም ሥርዐት ነው።’ ”


ይልቁን በጣዖት ከረከሰ ነገር፣ ከዝሙት ርኩሰት፣ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋ ከመብላትና ደም ከመመገብ እንዲርቁ ልንጽፍላቸው ይገባል፤


ለጣዖት ከተሠዋ ነገር፣ ከደም፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከዝሙት ርኩሰት እንድትርቁ ነው። ከእነዚህ ዐይነት ነገሮች ብትርቁ ለእናንተ መልካም ነው። ደኅና ሁኑ።


ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።


ታዲያ እግዚአብሔርን ለምን አልታዘዝህም? ለምርኮውስ ተስገብግበህ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ለምን አደረግህ?”