Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 14:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ስለዚህም ከጠላት ባገኙት ምርኮ ላይ እየተረባረቡ በጎችን፥ የቀንድ ከብቶችንና ጥጆችን ባገኙበት ቦታ እያረዱ ሥጋውን ከነደሙ መብላት ጀመሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 በምርኮው ላይ ተረባርበው በጉን፣ በሬውንና ጥጃውን በመውሰድ በመሬት ላይ ዐርደው ሥጋውን ከነደሙ በሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 በምርኮው ላይ ተረባርበው በጉን፥ በሬውንና ጥጃውን በመውሰድ በመሬት ላይ ዐርደው ሥጋውን ከነደሙ በሉት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ሕዝ​ቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎ​ችን፥ በሬ​ዎ​ች​ንም፥ ጥጆ​ች​ንም ወስ​ደው እን​ዳ​ገኙ በም​ድር ላይ አረዱ፤ ሕዝ​ቡም ከደሙ ጋር በሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ሕዝቡም ለምርኮ ሳሱ፥ በጎችን በሬዎችንም ጥጆችንም ወስደው በምድር ላይ አረዱ፥ ሕዝቡም ከደሙ ጋር በሉ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 14:32
11 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን በደሙ ውስጥ ሕይወት ስላለ ደም ያለበትን ሥጋ አትብሉ።


“እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ሥጋ ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ጣዖት ታመልካላችሁ፤ ግድያ ትፈጽማላችሁ፤ ታዲያ፥ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ እንዴት ምድሪቱ የእኛ ርስት ናት ትላላችሁ?


“ደም ያለበትን ሥጋ አትብሉ፤ የአስማትን ነገር አትከተሉ፤


ከእስራኤላውያን ወገን ስብ የሆነውን ሥጋ ወይም የእንስሶችን ደም የሚመገብ አይኑር፤ ይህም እስራኤላውያን በሚኖሩበት ዘመንና ቦታ ሁሉ ለዘለዓለሙ ተጠብቆ የሚኖር ቋሚ ሥርዓት ይሁን።


ይልቅስ ‘ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብን አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ሳይታረድና ደሙም ሳይፈስ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምንም አትብሉ’ ብለን እንጻፍላቸው።


ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብ አትብሉ፤ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምም አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ብትጠበቁ መልካም ታደርጋላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”


ነገር ግን ደማቸውን አትብላ፤ ደሙን እንደ ውሃ በመሬት ላይ አፍስሰው፤


ታዲያ ስለምን ትእዛዙን አልፈጸምክም? ለምርኮስ በመሳሳትና በመስገብገብ እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኝ ነገር ስለምን አደረግህ?”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos