Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 9:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “ነገር ግን ሕይወቱ፣ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን ደም ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፥ ምክንያቱም በደም ውስጥ ሕይወት አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ነገር ግን በደሙ ውስጥ ሕይወት ስላለ ደም ያለበትን ሥጋ አትብሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 9:4
15 Referencias Cruzadas  

ደሙን ግን እንዳትበላ ተጠንቀቅ፤ ደም ሕይወት ስለ ሆነ፣ ሥጋን ከነሕይወቱ አትብላ።


ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።


ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።


ይልቁን በጣዖት ከረከሰ ነገር፣ ከዝሙት ርኩሰት፣ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋ ከመብላትና ደም ከመመገብ እንዲርቁ ልንጽፍላቸው ይገባል፤


በየትኛውም ቦታ ብትኖሩ የማንኛውንም የወፍ ዘር ወይም የእንስሳ ደም አትብሉ።


ለጣዖት ከተሠዋ ነገር፣ ከደም፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከዝሙት ርኩሰት እንድትርቁ ነው። ከእነዚህ ዐይነት ነገሮች ብትርቁ ለእናንተ መልካም ነው። ደኅና ሁኑ።


“ ‘በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ፣ ሥብ ወይም ደም ከቶ አትብሉ፤ ይህ ለመጪው ትውልድ ሁሉ የተሰጠ የዘላለም ሥርዐት ነው።’ ”


እግዚአብሔር የፈጠረው ማንኛውም ነገር መልካም ነውና፤ በምስጋና ከተቀበሉትም የሚጣል ምንም ነገር የለም፣


“ ‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ሥጋ አትብሉ። “ ‘ጥንቈላ ወይም አስማት አትሥሩ።


ስለዚህ ጥቂት ሰዎች መርጠን ከተወዳጆቹ ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋራ ወደ እናንተ ለመላክ ሁላችንም ተስማምተናል፤


አንተ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ነህና የሞተውን ሁሉ አትብላ፤ ከከተሞችህ በአንዲቱ ለሚኖር መጻተኛ ስጠው፤ ይብላውም፤ ለውጭ አገር ሰው ሽጠው። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።


በምርኮው ላይ ተረባርበው በጉን፣ በሬውንና ጥጃውን በመውሰድ በመሬት ላይ ዐርደው ሥጋውን ከነደሙ በሉት።


ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ዐይኖቻችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምም ታፈስሳላችሁ፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን ልትወርሱ ታስባላችሁ?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios