መዝሙር 97:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ስለ ትክክለኛ ፍርድህ የጽዮን ሕዝብ ደስ ይላቸዋል፤ የይሁዳ ከተሞችም ሐሤት ያደርጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ፍርድህ፣ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፤ የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፥ ተራሮች ደስ ይበላቸው፥ |
“እኔ እግዚአብሔር ጽዮንንና ባድማ የሆኑባትን ቦታዎችዋን ሁሉ አጽናናለሁ፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔደን፥ በረሓዋንም እንደ ገነት አደርጋለሁ፤ በእርስዋም ተድላና ደስታ ይገኛል፤ እንዲሁም የምስጋና መዝሙር ድምፅ ይሰማል።
እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ እንዲህ ብሎ ያውጃል፦ “አዳኝሽ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር ለሰዎች የሚከፍለው ዋጋና ሽልማት አለ ብላችሁ ለጽዮን ልጅ ንገሩአት።”
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!