La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 90:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዘመናችን ሁሉ በቊጣህ ያልፋሉ የዕድሜአችንም ፍጻሜ እንደ እስትንፋስ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዘመናችን ሁሉ በቍጣህ ዐልፏልና፤ ዕድሜያችንንም በመቃተት እንጨርሳለን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፥ እኛም በመዓትህ አልቀናልና፥ ዘመኖቻችንንም እንደ ትንፋሽ ይሆናሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ፥ አንተ ተስ​ፋዬ ነህና፤ ልዑ​ልን መጠ​ጊ​ያህ አደ​ረ​ግህ።

Ver Capítulo



መዝሙር 90:9
5 Referencias Cruzadas  

የእግዚአብሔር መልአክ ሲያሳድዳቸው፤ በነፋስ እንደሚበተን ገለባ ይሁኑ!


እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ ሳለቅስም ቶሎ ብለህ እርዳኝ፤ እኔ ለጥቂት ጊዜ የአንተ እንግዳ ነኝ፤ እንደ ቀድሞ አባቶቼም በስደተኛነት የምኖር ነኝ።


የዘመኔን መለኪያ ከእጅ መዳፍ እንዳይበልጥ አድርገህ አሳጠርከው፤ ዕድሜዬም በአንተ ፊት ከምንም አይቈጠርም፤ በእርግጥ የሰው ሕይወት እንደ ነፋስ ሽውታ ነው።


ስለዚህ ዕድሜአቸውን እንደ እስትንፋስ አሳጠረ፤ ሕይወታቸውም በሽብር እንዲያልቅ አደረገ።


ለአንተ አንድ ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን ነው፤ አልፎ እንደ ሄደው እንደ ትናንት ነው፤ እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓቶች ነው።