መዝሙር 88:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ መከራ ስለ ደረሰብኝ ለመሞት ተቃርቤአለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴ በመከራ ተሞልታለችና፤ ሕይወቴም ወደ ሲኦል ተቃርባለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ፥ ለባሪያዬም ለዳዊት ማልሁ፥ |
እግዚአብሔር ሆይ! ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርብልህን ጸሎት ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በሽንገላ ሳይሆን በእውነት የማቀርበውን ጸሎት ስማ።
በችግር ጊዜ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ሌሊቱን ሙሉ ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ይሁን እንጂ ለመጽናናት አልቻልኩም።
እርሱም በሌሎች የተናቀና የተጠላ ነበር፤ እርሱ የመከራና የሐዘን ሰው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እስኪያዞሩበት ድረስ እርሱ የተናቀ፥ እኛም ያላከበርነው ሰው ነበር።