መዝሙር 73:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ምንም ሕመም ስለሌለባቸው፥ ሰውነታቸው ጤናማና ወዛም ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳች ጣር የለባቸውም፤ ሰውነታቸውም ጤናማና የተደላደለ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሞታቸው ስቃይ የለውምና፥ ሰውነታቸውም ጤናማ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶችህ በበዓልህ መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ። |
እግዚአብሔር ሆይ! የሕይወታቸው ድርሻ የዚህ ዓለም ነገር ብቻ ከሆነ ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ለምትወዳቸው ምግብን ስጣቸው፤ ልጆቻቸው ብዙ ይኑራቸው፤ የልጅ ልጆቻቸውም የተትረፈረፈ ምግብ እንዲኖራቸው አድርግ።
ጥበበኛንም ሆነ ሞኝን ሁለቱንም ለረጅም ጊዜ የሚያስታውሳቸው አይገኝም፤ በሚመጣው ዘመን ሁላችንም የተረሳን ሆነን እንቀራለን፤ ጥበበኞችም ሆንን ሞኞች፥ ሁላችንንም ሞት ይጠብቀናል።
እነርሱ እንደ ቅልብ ሰንጋ ወፍረዋል፤ ክፉ ሥራቸውም ገደብ የለሽ ሆኖአል፤ እናትና አባት የሌላቸውን ልጆች መብት አያስከብሩም፤ ለችግረኞችም ትክክለኛ ፍርድ አይፈርዱም።