Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 17:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነርሱ ለርኅራኄ ልባቸውን ዘግተዋል፤ አፋቸውም ትዕቢትን ይናገራል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ደንዳና ልባቸውን ደፈኑት፤ በአፋቸውም ትዕቢት ይናገራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አንጀታቸውን በስብ ቋጠሩ፥ በአፋቸውም ትንቢትን ተናገሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በኪ​ሩ​ቤ​ልም ላይ ተቀ​ምጦ በረረ፥ በነ​ፋ​ስም ክንፍ በረረ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 17:10
15 Referencias Cruzadas  

እስቲ በመታበይ አትጓደዱ፤ የትምክሕት ንግግራችሁንም አስወግዱ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን ያውቃል፤ ሕዝብ የሚሠራውንም ሁሉ በፍርድ ይመዝናል።


በትዕቢተኞች ብዙ መዋረድ፥ በትምክሕተኞችም ብዙ መናቅ ደርሶብናል።


በጻድቅ ላይ በትዕቢትና በንቀት በኩራትም ስለሚናገር የሐሰት አንደበታቸውን ጸጥ አሰኝ።


የእዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸው ተደፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተጨፍነዋል፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥ በዐይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸውም ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ወደ እኔ በተመለሱና በፈወስኳቸው ነበር።’


በስሕተት ከሚኖሩት ሰዎች መካከል አምልጠው ከመጡ ገና ብዙ ያልቈዩትን ሰዎች ከንቱ የሆነ የዕብሪት ቃል በመናገር፥ በሥጋዊ ፍትወትና በሴሰኛነት በማባበል ያታልሉአቸዋል።


የእነዚህ ሰዎች ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸውም ተጨፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተዘግቶአል፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥ በዐይናቸው አይተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ወደ እኔ በተመለሱና እኔም በፈወስኩአቸው ነበር።’


ቀጥሎም “እንዳያዩ፥ እንዳይሰሙና እንዳያስተውሉ በዓይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ ተመልሰው እንዳይፈወሱ ይህን ሕዝብ ልቡ የደነደነ፥ ጆሮው የተደፈነ፥ ዐይኑም የተጨፈነ እንዲሆን አድርግ” አለኝ።


እነርሱ ትዕቢተኞችና ስሜተ ቢሶች ናቸው፤ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል።


ፊቱ በስብ ተሸፍኖአል ወገቡም በውፍረት ተድቦልብሎአል።


‘ጠላትማ አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፤ ሀብታቸውንም እካፈላለሁ፤ የፈለግኹትንም እወስዳለሁ፤ ሰይፌንም መዝዤ አጠፋቸዋለሁ’ ብሎ ነበር፤


ንጉሡም “ለመሆኑ እግዚአብሔር ማን ነው? የእርሱንስ ትእዛዝ ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ።


“እስራኤላውያንም ወፈሩ፤ ዐመፁም። በጣም በልተው ወፈሩ፤ ሰቡ፤ የፈጠራቸውንም አምላክ ተዉ፤ መጠጊያ አዳኛቸውን አቃለሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios