እግዚአብሔርን በመዝሙር አመሰግነዋለሁ፤ በምስጋናም መዝሙር ታላቅነቱን እገልጣለሁ።
የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አወድሳለሁ፤ በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
እኔ ችግረኛና ቁስለኛ ነኝ፥ አቤቱ፥ መድኃኒትህ ያቁመኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ሰማኸኝና ስላዳንከኝ አመሰግንሃለሁ።
እግዚአብሔር ኀይሌና ጋሻዬ ነው፤ ስለሚረዳኝና ደስ ስለሚያሰኘኝም በእርሱ እተማመናለሁ፤ በመዝሙሮቼም አመሰግነዋለሁ።
የእግዚአብሔርን ታላቅነት ከእኔ ጋር አስታውቁ፤ በኅብረትም ስሙን እናክብር።
የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ ስእለትህንም ለልዑል ስጥ።