አምላክ ሆይ! በጽዮን ሆነን አንተን ማመስገን፤ ለአንተ የተሳልነውንም መስጠት ይገባናል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በጽዮን ለአንተ ውዳሴ ይገባል፤ ለአንተ ስእለት ይፈጸማል።
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
በምድር ያላቸሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥
ዳዊትም ሄዶ በምሽጉ ውስጥ ስለ ኖረ ያቺ ስፍራ “የዳዊት ከተማ” ተብላ ተጠራች።
ታቦቱ ወደ ከተማይቱ በመግባት ላይ ሳለ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ንጉሥ ዳዊት በደስታ ሲያሸበሽብና ሲዘል በመስኮት ተመለከተች፤ በልብዋም ናቀችው።
እግዚአብሔር ሆይ! ልዕልናህ ከፍ ከፍ ይበል፤ ስለ ታላቁ ኀይልህም የምስጋና መዝሙር እናቀርባለን።
አምላክ ሆይ! እኔ ራሴ ለአንተ የስእለት ግዴታ ገብቼአለሁ፤ ስእለቴን ከምስጋና መሥዋዕት ጋር አቀርባለሁ።
የሚያድነኝ እርሱ ብቻ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።
መፈራት ለሚገባው ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ተስላችሁ የተሳላችሁትን ስእለት ፈጽሙ፤ እናንተ በቅርብ ያላችሁ ሕዝቦች መባ አምጡለት።
ቤቱን በሳሌም (ኢየሩሳሌም) አደረገ፤ በጽዮንም ተራራ ላይ ይኖራል።