መዝሙር 37:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤ እግዚአብሔር የረገማቸው ግን ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤ እርሱ የሚረግማቸው ግን ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱን የሚባርኩት ምድርን ይወርሳሉና፥ የሚረግሙት ግን ይጠፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ የመድኀኒቴ አምላክ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን። |
ርዳታ ለማግኘት በምትጮኹበት ጊዜ እስቲ የሰበሰባችኋቸው ጣዖቶቻችሁ ያድኑአችሁ! እነርሱን የነፋስ ሽውታ ያስወግዳቸዋል፤ እስትንፋስም ይወስዳቸዋል፤ በእኔ የሚተማመን ግን ምድሪቱ የእርሱ ትሆናለች፤ የተቀደሰ ተራራዬንም ርስት ያደርጋል።”
ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!
“በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ትእዛዞች ሁሉ ጸንቶ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ “ሕግን በመፈጸም እንጸድቃለን” የሚሉ ሁሉ የተረገሙ ናቸው።
“በእንጨት ላይ ተሰቅሎ የሚሞት ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ ክርስቶስ ስለ እኛ እንደ ተረገመ ሰው ሆኖ ሕግ ከሚያስከትለው ርግማን ዋጀን።