መዝሙር 37:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው ደጉን ሰው ለማጥፋት ያሳድምበታል፤ በጥላቻም ጥርሱን ያፋጭበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች በጻድቃን ላይ ያሤራሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ በጻድቁ ላይ ያደባል፥ ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያንገጫግጫል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴንም የሚሹአት በረቱብኝ፥ መከራዬንም የሚፈልጉ ከንቱን ተናገሩ፥ ሁልጊዜም ያጠፉኝ ዘንድ በሽንገላ ይመክራሉ። |
በተለይም መርዶክዮስ አይሁዳዊ መሆኑን በተረዳ ጊዜ መርዶክዮስን ብቻ መግደል በቂ እንዳልሆነ ተገነዘበ፤ ስለዚህም በመላው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ውስጥ ያሉትን የመርዶክዮስ ወገን የሆኑትን አይሁድን ሁሉ ለማጥፋት ዕቅድ አወጣ።
ነገር ግን ያን አይሁዳዊ መርዶክዮስን በቤተ መንግሥቱ መግቢያ በር አጠገብ ተቀምጦ በማየቴ ይህ ሁሉ ክብር ለእኔ ምንም ትርጒም ሊሰጠኝ አልቻለም።”
በክፋት ምክንያት ሠራዊቱና መደበኛው የሚቃጠል መሥዋዕት ለእርሱ ተሰጠ፤ እርሱም እውነትን ወደ መሬት ጣለ፤ የሚያደርገውም ነገር ሁሉ እየተሳካለት ሄደ።
ይህም ንጉሥ እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በራሱ ኀይል አይደለም፤ እጅግ አሠቃቂ የሆነ ጥፋት ይፈጽማል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፤ በኃያላን ሰዎችና በተቀደሱት ሕዝብ ላይ ጥፋትን ያስከትላል።
ክፉ ሥራ ለመሥራት ለሚያቅዱና በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን በሥራ ላይ ያውሉታል።
በልቡም “ሜልኮልን ለዳዊት እሰጣለሁ፤ እርስዋም ዳዊትን እንድታጠምድልኝ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ በፍልስጥኤማውያን እጅ ይገደላል” ሲል አሰበ። ስለዚህም ሳኦል ለሁለተኛ ጊዜ ዳዊትን ጠርቶ “አሁን የእኔ ዐማች ትሆናለህ” አለው።