La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 148:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገሥታትና የምድር ሕዝቦች፥ መሳፍንትና ፈራጆች ሁሉ አመስግኑት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣ መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የምድር ነገሥታትና አሕዛብ ሁሉ፥ አለቆችና የምድር ፈራጆች ሁሉ፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የም​ድር ነገ​ሥ​ታት፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ፥ አለ​ቆች፥ የም​ድ​ርም ፈራ​ጆች ሁሉ፤

Ver Capítulo



መዝሙር 148:11
12 Referencias Cruzadas  

አሕዛብ የእግዚአብሔርን ስም የምድር ነገሥታትም አንተን ይፈራሉ።


አንተ የፈጠርካቸው ሕዝቦች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ለአንተም ይሰግዳሉ፤ የአንተንም ስም ያከብራሉ።


ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል። የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቂአለሽ፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት የሚጠባበቁ ከቶ አያፍሩም።”


ሕዝቦች ወደ ብርሃንሽ፥ ነገሥታትም ወደ ንጋትሽ ወገግታ ይመጣሉ።


ሕዝቦች በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፤ የምድር ነገሥታትም ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤