የእግዚአብሔር ኀይል ከፍ ከፍ አለ፤ ኀይሉም ድል አድራጊ ነው።
የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለች፤ የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች።”
የጌታ ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አደረገችኝ፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይሉን አከናወነ።
ትእዛዞችህን አነብባለሁ፤ ቃልህንም አልረሳም።
“አምላክ ሆይ፥ የቀኝ እጅህ ኀይል፥ ባለ ግርማ ነው፤ ጠላትን ሰባብሮ ይጥላል፤