መዝሙር 115:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤ እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤ ድምፅም ማሰማት አይችሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤ እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤ በጕሮሯቸውም ድምፅ አይፈጥሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጅ አላቸው አይዳስሱምም፥ እግር አላቸው አይሄዱምም፥ በጉሮሮአቸውም ድምፅ አያሰሙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ እኔ ባሪያህ ነኝ፥ ባሪያህ ነኝ፥ የሴት ባሪያህም ልጅ ነኝ፤ ሰንሰለቴን ሰበርህ። |
አንዳንድ ሰዎች ኰረጆአቸውን ከፍተው ወርቅ እንደ ልባቸው ይመዛሉ፤ ብሩንም በሚዛን ይመዝናሉ፤ ጣዖት አድርጎ እንዲሠራላቸውም አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ ከተሠራም በኋላ እየሰገዱ ያመልኩታል።
በማግስቱም ማለዳ የአሽዶድ ሰዎች ተነሥተው ሲመለከቱ የዳጎን ምስል ሐውልት በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ አዩት፤ ከዚያም አንሥተው ቀድሞ በነበረበት ስፍራ አቆሙት፤