“እኔ ግን ከትቢያ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤ ታዲያ አንተ እንደ ኢዮርብዓም ኃጢአት ሠራህ፤ ሕዝቤንም ወደ ኃጢአት መራህ፤ የኃጢአታቸውም ብዛት የእኔን ቊጣ አነሣሥቶአል፤
መዝሙር 113:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድኾችን ከትቢያ ችግረኞችንም ከዐመድ ቊልል ያነሣቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድኻውን ከዐፈር ያነሣል፤ ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመኰንኖች ጋር ከሕዝቡም መኰንኖች ጋር ያኖረው ዘንድ ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከያዕቆብ አምላክ ፊት፥ ከእግዚአብሔር ፊት ምድር ተናወጠች፤ |
“እኔ ግን ከትቢያ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፤ ታዲያ አንተ እንደ ኢዮርብዓም ኃጢአት ሠራህ፤ ሕዝቤንም ወደ ኃጢአት መራህ፤ የኃጢአታቸውም ብዛት የእኔን ቊጣ አነሣሥቶአል፤
ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤ እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ! አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል።
በምድሪቱ ያሉ ዛፎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ ረጃጅም ዛፎችን አሳጥራለሁ፤ አጫጭር ዛፎችንም ከፍ ብለው እንዲያድጉ አደርጋለሁ፤ እኔ ለምለም ዛፎችን አደርቃለሁ፤ ደረቅ ዛፎችንም አለመልማለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ አደርጋለሁ ያልኩትንም ሁሉ እፈጽማለሁ።”
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?
እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ ማንን ለመግደል እንደሚጥር ተመልከት! ማንንም እንደሚያሳድድ አስተውል! የሞተ ውሻን ወይስ ቁንጫን? ማንን እንደሚያሳድድ ተመልከት!