እንደገናም በበረሓው ብዙ ኲሬዎች እንዲኖሩ፥ በደረቁም ምድር ብዙ ምንጮች እንዲገኙ አደረገ።
ምድረ በዳውን ወደ ውሃ መከማቻ፣ ደረቁንም ምድር ወደ ውሃ ምንጭ ቀየረ።
ምድረ በዳን ወደ ውኃ ማጠራቀምያ፥ ደረቁንም ምድር ወደ ውኃ ምንጭነት ቀየረ።
ዝናብ እንዲዘንብ የሚያደርግ ማነው? ጠፍና ባድማ የሆነውን መሬት ረስርሶ ምድሩንም ሣር እንዲያበቅል ያደረገው ማነው?
እርሱ አለቱን ወደ ኩሬ ውሃ፥ ጭንጫውንም ሸንተረር ወደ ወራጅ ምንጭ ይለውጣል።
ምንጭን ከአለት አፈለቀ፤ ውሃውም እንደ ወንዝ እንዲፈስስ አደረገ።