መዝሙር 104:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነዚህም ምንጮችና ወንዞች አጠገብ ባሉት ዛፎች ላይ፥ ወፎች ጎጆአቸውን ሠርተው ያዜማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰማይ ወፎች ጐጇቸውን በወንዞቹ ዳር ይሠራሉ፤ በቅርንጫፎችም መካከል ይዘምራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰማይም ወፎች በእነርሱ ዘንድ ያድራሉ፥ በቅጠሎች መካከል ያዜማሉ ይጮኻሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ በቍጥር እጅግ ጥቂቶችና፥ በውስጧ ስደተኞች ሲሆኑ። |
ንጉሤና አምላኬ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ድንቢጦች ለመኖሪያቸው ጎጆ ሠርተዋል፤ ዋኖሶችም ጫጩቶቻቸውን የሚያኖሩበት በመሠዊያዎችህ አጠገብ ቤት አላቸው።
እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?
ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ በአየር ላይ የሚበሩ ወፎችም የሚሰፍሩበት ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ስፍራ የለውም” ሲል መለሰለት።