“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
ምሳሌ 22:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብልኅ ሰው አደጋ ሲመጣ አይቶ ይሸሸጋል። ማስተዋል የጐደለው ሰው ግን ሰተት ብሎ ወደ መከራ በመግባት ይጐዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስተዋይ ክፉን አይቶ ራሱን ይሸሽጋል፤ አላዋቂዎች ግን በዚያው ይቀጥላሉ፤ ይቀጡበታልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፥ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይሄዱና ይጐዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐዋቂ ሰው ክፉ ሰው በኀይል ሲቀጣ አይቶ ይገሠጻል፥ አላዋቂዎች ግን ሲያልፉ ይጐዳሉ። |
“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ።
በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።