የሌላ ሰው ዕዳ ለመክፈል ዋስ አትሁን፤
በዋስትና ቃል እጅ አትምታ፤ ለብድር ተያዥ አትሁን፤
የምር ቃል እንደሚገቡ፥ ለባለ ዕዳዎች እንደሚዋሱ አትሁን፥
የሰውን ፊት በማፈር ራስህን ለዋስትና አትስጥ።
የማታውቀውን ሰው ዕዳ ለመክፈል ዋስ ብትሆን፥ በችግር ላይ ትወድቃለህ፤ ዋስ መሆን ቢቀርብህ ግን የተሻለ ነው።
ማስተዋል የጐደለው ሰው ለሌላ ሰው ዋስ ይሆናል፤ ራሱንም ተያዥ አድርጎ ይሰጣል።
ማንም ሰው ለእንግዳ ሰው ከተዋሰ ልብሱን ውሰድ፤ ለማይታወቅ ሰው መያዣ እንዲሆን አንተ ዘንድ አስቀምጠው።