ዮሴፍ የግብጽ ምድር አስተዳዳሪ በመሆኑ ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ እህል እንዲሸጥላቸው ያደርግ ነበር፤ ስለዚህ የዮሴፍ ወንድሞች ወደ እርሱ መጡና ግንባራቸው መሬት እስኪነካ ዝቅ ብለው እጅ ነሡት።
ምሳሌ 11:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቈይቶ በውድ ዋጋ ለመሸጥ እህሉን የሚያከማች ሰው፥ በሕዝብ ዘንድ የተረገመ ይሆናል፤ እህሉን ለገበያ የሚያቀርብ ሰው ግን፥ በሕዝብ ዘንድ የተመሰገነ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድብቅ እህል የሚያከማቸውን ሕዝብ ይረግመዋል፤ አውጥቶ የሚሸጥ ግን በረከት ይጐናጸፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እህልን የሚደብቅ ሰው በሕዝብ ዘንድ ይረገማል፥ በረከት ግን በሚሸጠው ራስ ላይ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስንዴውን የሚያደልብ ለአሕዛብ ይተወዋል። በረከት ግን በሚሰጥ ሰው ራስ ላይ ነው። |
ዮሴፍ የግብጽ ምድር አስተዳዳሪ በመሆኑ ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ እህል እንዲሸጥላቸው ያደርግ ነበር፤ ስለዚህ የዮሴፍ ወንድሞች ወደ እርሱ መጡና ግንባራቸው መሬት እስኪነካ ዝቅ ብለው እጅ ነሡት።