በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ በደሌንም ከአንተ አልሰወርኩም፤ ኃጢአቴን ሁሉ ለአንተ ለመናዘዝ ወሰንኩ፤ አንተም ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር አልክልኝ።
ዘኍል 5:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአቱን ይናዘዝ፤ ስለ በደል ሊከፈል በሚገባው ዋጋ ላይ ከመቶ ኻያ እጅ በመጨመር ለተበደለው ሰው ካሳ ይስጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሠራው ኀጢአት ይናዘዝ፤ ስለ በደሉም ሙሉ ካሳ ይክፈል፤ የተመደበበትም ካሳ ላይ አንድ ዐምስተኛ በመጨመር በደል ላደረሰበት ሰው ይስጥ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራውንም ኃጢአት ይናዘዝ፤ የወሰደውንም በሙሉ ይመልስ፥ በእርሱም ላይ አምስት እጅ ይጨምርበት፥ ለበደለውም ሰው ይስጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያች ሰውነት ብትናዘዝ፥ ያደረገችውንም ኀጢአት ሁሉ ብትናገር የወሰደውን ዓይነቱን ሁሉ ይመልስ። አምስተኛ እጅም ለባለ ገንዘቡ ይጨምር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወሰደውንም በሙሉ ይመልስ አምስተኛውንም ይጨምርበት፥ ለበደለውም ሰው ይስጠው። |
በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ በደሌንም ከአንተ አልሰወርኩም፤ ኃጢአቴን ሁሉ ለአንተ ለመናዘዝ ወሰንኩ፤ አንተም ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር አልክልኝ።
“አንድ ሰው ለእግዚአብሔር መክፈል የሚገባውን ባለመክፈል ሳያውቅ በደል ቢፈጽም፥ ለእግዚአብሔር የበደል መሥዋዕት የሚሆን ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ያምጣ፤ ወይም በቤተ መቅደሱ ሚዛን መሠረት ዋጋው ተገምግሞ ይክፈል። ይህም የበደል መሥዋዕት ነው።
ቀድሞ መስጠት ይገባው ከነበረው ጋር አንድ አምስተኛ ጨምሮ ያምጣ፤ እርሱንም አምጥቶ ለካህኑ ይስጥ፤ ካህኑም እንስሳውን ስለ ሰውየው ኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርበው፤ በደል የሠራውም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።
“ስለ ኃጢአት ስርየት በሚቀርበው መሥዋዕትና ስለ በደል ስርየት በሚቀርበው መሥዋዕት መካከል ለሁለቱም የሚሠራ አንድ ዐይነት ሕግ አለ፤ ይኸውም የእንስሳው ሥጋ መሥዋዕቱን ለሚያቀርበው ካህን ምግብ እንዲሆን ይሰጣል፤
ያ ሰው ቢሞትና ካሳውንም የሚቀበልለት የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ግን በካህኑ አማካይነት ስጦታው ለእግዚአብሔር ሆኖ ለካህኑ ይሰጥ፤ ይህም ስለ በደል የሚከፈል ዋጋ መሰጠት ያለበት፥ በደል የሠራው ሰው ለኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕትነት ከሚያቀርበው አውራ በግ ጋር ተጨማሪ በመሆን ነው።
ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታ ኢየሱስን እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! እነሆ፥ ካለኝ ሀብት ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ በማታለል ከሰው ላይ የወሰድኩትም ገንዘብ ቢኖር፥ አራት እጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ።”