ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው።
ዘኍል 33:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች ስሞች ሙሴ በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት ጻፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም በጕዟቸው ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸውን ቦታዎች በእግዚአብሔር ትእዛዝ መዘገበ፤ በየቦታው እየሰፈሩ ያደረጉት ጕዞም ይህ ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በጌታ ትእዛዝ የጉዞአቸው መነሻ የሆኑትን ስፍራዎቻቸውን ጻፈ፤ እንደ መነሻ ስፍራዎቻቸው ጉዞአቸው እንዲህ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ተጓዙ የሰፈሩበትን ጻፈ፥ እየተጓዙ ያደሩበት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ጕዞአቸው አወጣጣቸውን ጻፈ፤ እንደ አወጣጣቸውም ጕዞአቸው እንዲህ ነበረ። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው።
ለሁለተኛ ጊዜ የማስጠንቀቂያውን ድምፅ ስታሰማ በስተደቡብ የሰፈሩት ሰፋሪዎች ጒዞ ይጀምሩ፤ በዚህም ዐይነት የማስጠንቀቂያ የመለከት ድምፅ የሚነፋው፥ ሰፈር ለቆ ጒዞ በሚጀመርበት ጊዜ ይሆናል።
እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ከወጡ በኋላ በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች የሚያስረዳው ታሪክ ይህ ነው፦
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር የወጡት የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ማለትም በመጀመሪያው የፋሲካ በዓል ማግስት ነበር። ግብጻውያን ሁሉ ፊት ለፊት እያዩአቸው በእግዚአብሔር ጠባቂነት የራምሴን ከተማ ለቀው ወጡ፤