ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።
ዘኍል 21:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞአብ ሆይ! ወዮልሽ! እናንተ የከሞሽ ሰዎች ሆይ! ትደመሰሳላችሁ፤ ወንዶች ልጆቹን ስደተኞች እንዲሆኑ አደረጋቸው፤ ሴቶች ልጆቹንም ንጉሥ ሲሖን እንዲማረኩ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ሆይ፤ ተደመሰስህ! ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፣ ሴቶች ልጆቹን ለምርኮ፣ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን አሳልፎ ሰጥቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞዓብ ሆይ! ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ሆይ! ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፥ ሴቶች ልጆቹንም ለምርኮ፥ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የካሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቻቸውን ለማደን፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለምርኮ፤ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የከሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፥ ሴቶች ልጆቹንም ለምርኮ፥ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ። |
ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።
ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ አጸያፊዎች ለሆኑት ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን አዘጋጀላቸው።
እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኲሰት ተራራ በስተ ደቡብ ዐስታሮት ተብላ ለምትጠራው ለሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአብ አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞን አምላክ ንጉሥ ሰሎሞን አሠርቶአቸው የነበሩት አጸያፊዎች ምስሎች ሁሉ የረከሱ መሆናቸውን አስገነዘበ።
ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።
የአርኖንን ወንዝ የሚሻገሩ የሞአብ ሴቶች ከጎጆዎቻቸው ተበታትነው ክንፎቻቸውን እያራገቡ ወዲያና ወዲህ እንደሚንከራተቱ የወፍ መንጋዎች ናቸው።
በሽሽት የደከሙ ስደተኞች በሐሴቦን ጥላ ሥር ተጠልለዋል፤ ይህም የሆነው እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሲሆን ቤቶች ወጥቶ የሞአብን ግንባር ቀደም ሠራዊትና ደጋፊ መሪዎችዋን አቃጥሎአል።
“የሞአብ ሕዝብ ሆይ! በኀይላችሁና በሀብታችሁ ብዛት ተማምናችሁ ነበር፤ አሁን ግን እነሆ እናንተ ራሳችሁ እንኳ ትማረካላችሁ፤ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራው ጣዖት ከልዑላን መሳፍንትና ከካህናቱ ጋር ተማርኮ ይወሰዳል።
አየዋለሁ፤ ነገር ግን አሁን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፤ ግን በቅርብ አይደለም፤ ኮከብ ከያዕቆብ፥ በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይወጣል። የሞአብን ድንበር፥ የሴትንም ዘሮች ሁሉ ይደመስሳል።