ለእግዚአብሔርም መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ አቀረበ፤ እግዚአብሔርም የዳዊትን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የወረደውም የቸነፈር መቅሠፍት ከዚህ በኋላ ቆመ።
ዘኍል 16:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም መቅሠፍቱ እንዲቆም አደረገ፤ አሮንም በሞቱትና በሕይወት ባሉት መካከል ቆሞ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በሕይወት ባሉትና በሞቱት መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተከለከለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሙታንና በሕያዋን መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተገታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሙታንና በሕያዋን መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተከለከለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሙታንና በሕያዋን መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተከለከለ። |
ለእግዚአብሔርም መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ አቀረበ፤ እግዚአብሔርም የዳዊትን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የወረደውም የቸነፈር መቅሠፍት ከዚህ በኋላ ቆመ።
አሮንም በመታዘዝ ጥናውን ይዞ ወደ ተሰበሰበው ሕዝብ መካከል ፈጥኖ ሄደ፤ መቅሠፍቱ እንደ ጀመረ በተመለከተ ጊዜ ዕጣኑን በፍሙ ላይ አድርጎ ለሕዝቡ አስተሰረየላቸው፤
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሰውየውን በቤተ መቅደስ አገኘውና “እነሆ፥ አሁን ድነሃል፤ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይደርስብህ ከእንግዲህ ወዲህ ኃጢአት አትሥራ” አለው።
እንዲሁም እግዚአብሔር ከሞት ያስነሣውን፥ ከሚመጣው ቊጣ የሚያድነንን፥ የልጁን የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት እንዴት እንደምትጠባበቁም ይመሰክራሉ።
ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤