እነርሱም ሁሉ ለበዓሉ የሚሆኑትን አንድ መቶ ወይፈኖችን፥ ሁለት መቶ በጎችንና አራት መቶ ጠቦቶችን ለመሥዋዕት አቀረቡ፤ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆኑም ዐሥራ ሁለት ፍየሎችን በእያንዳንዱ ነገድ ስም አቀረቡ።
ዘኍል 15:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ ዐይነቱ ስሕተት የተፈጸመው በማኅበሩ አለማወቅ ከሆነ አንድ ወይፈን አምጥተው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት፤ ከእርሱም ጋር ተገቢውን የእህልና የወይን ጠጅ ቊርባን ያቅርቡ፤ በተጨማሪም አንድ ተባዕት ፍየል ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የተፈጸመው ሆነ ተብሎ ሳይሆንና ማኅበረ ሰቡም ሳያውቀው ከሆነ፣ ማኅበረ ሰቡ በሙሉ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አድርጎ አንድ ወይፈን በእሳት ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚሁም ጋራ ሥርዐቱ የሚጠይቀውን የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን ደግሞም ለኀጢአት መሥዋዕት ተባዕት ፍየል ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም ነገር ማኅበሩ ሳያውቀው በስሕተት የተደረገ ቢሆን፥ ማኅበሩ ሁሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ከእህሉ ቁርባንና ከመጠጡ ቁርባን ጋር እንደ ሕጉ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን አንድ ወይፈን፥ ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ያቅርብ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማኅበሩም ፊት ያልታወቀ ኀጢአት ቢኖር፥ ማኅበሩ ሁሉ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ከመንጋዎች አንድ ንጹሕ ወይፈን ያቀርባሉ። የእህሉ ቍርባንና የመጠጡ ቍርባንም እንደ ሕጉ ነው፤ ለኀጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀርባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኅበሩ ሳያውቁ በስሕተት ቢደረግ፥ ማኅበሩ ሁሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር እንደ ሕጉ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን አንድ ወይፈን፥ ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀርባሉ። |
እነርሱም ሁሉ ለበዓሉ የሚሆኑትን አንድ መቶ ወይፈኖችን፥ ሁለት መቶ በጎችንና አራት መቶ ጠቦቶችን ለመሥዋዕት አቀረቡ፤ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆኑም ዐሥራ ሁለት ፍየሎችን በእያንዳንዱ ነገድ ስም አቀረቡ።
ከዚያም ቀጥሎ እነዚያ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን መባ ሁሉ አመጡ፤ በዚህ ዐይነት በመላው እስራኤል ሕዝብ ስም ዐሥራ ሁለት ኰርማዎችን፥ ዘጠና ስድስት የበግ አውራዎችንና ሰባ ሰባት የበግ ጠቦቶችን አቀረቡ፤ እንዲሁም ስለ ኃጢአታቸው ስርየት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎችን አቀረቡ፤ እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ።
ከዚያም ቀጥሎ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አንድ ተባዕት ፍየል፤ ለአንድነት መሥዋዕት የአንድ ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤
“ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ማንም ሰው ተሳስቶ ኃጢአት ቢሠራ ወይም ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዱን ቢተላለፍ ከዚህ የሚከተለውን ሥርዓት ይጠብቅ፦
“አንድ ሰው ለእግዚአብሔር መክፈል የሚገባውን ባለመክፈል ሳያውቅ በደል ቢፈጽም፥ ለእግዚአብሔር የበደል መሥዋዕት የሚሆን ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ያምጣ፤ ወይም በቤተ መቅደሱ ሚዛን መሠረት ዋጋው ተገምግሞ ይክፈል። ይህም የበደል መሥዋዕት ነው።
ከመንጋው ምንም ነውር የሌለበት ተባዕት በግ ስለ በደሉ መሥዋዕት አድርጎ ወደ ካህን ያምጣ፤ ዋጋውም ተገምግሞ በይፋ በታወቀው ተመን ይወሰን፤ ካህኑም የእንስሳውን መሥዋዕት ስለዚያ ሰው ያቅርብ፤ በደል የሠራውም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።
ሁሉም በአንድነት የስሕተቱ ተካፋዮች ስለ ሆኑ መላው የእስራኤል ማኅበርና በእነርሱም መካከል የሚኖሩ መጻተኞች ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል።