እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣሉ፦ “በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቀሩት እስራኤላውያን ወገኖቻችን ጋር ሞተን ቢሆን መልካም በሆነ ነበር።
ዘኍል 14:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ ልኮአቸው ከነበሩት ሰዎች፥ ሄደው ከተመለሱ በኋላ ስለምድሪቱ ክፉ ወሬ በማውራት ሕዝቡን እንዲያጒረመርም ያደረጉት አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ ልኳቸው የነበሩትና ከዚያ ተመልሰው ስለ ምድሪቱ ክፉ ወሬ በማሠራጨት ማኅበረ ሰቡ በሙሉ እንዲያጕረመርሙበት ያደረጉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱንም እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች፥ እነርሱም ተመልሰው ስለ ምድሪቱ ክፉ ወሬ በማውራት በእርሱ ላይ ማኅበሩ ሁሉ እንዲያጉረመርሙ ያደረጉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሙሴ ልኮአቸው የተመለሱት ሰዎች ስለ እርስዋ በማኅበሩ ሁሉ ፊት አጕረመረሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሙሴ ልኮአቸው የተመለሱት ሰዎች ክፉ ወሬም ስለ ምድሪቱ እያወሩ በእርሱ ላይ ማኅበሩ ሁሉ እንዲያጕረመርሙ ያደረጉ፥ |
እንዲህ በማለት ከሙሴ ጋር ተጣሉ፦ “በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ለፊት ከቀሩት እስራኤላውያን ወገኖቻችን ጋር ሞተን ቢሆን መልካም በሆነ ነበር።