ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝቦቹን ለማጥፋት ዐቅዶ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የመረጠው ሙሴ በመካከል በመቆም፥ እንዳያጠፋቸውና ቊጣውንም እንዲመልስ እግዚአብሔርን ለመነ።
ዘኍል 14:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በጠየቅኸው መሠረት ይቅር እላቸዋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “በጠየቅኸው መሠረት ይቅር ብያቸዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዲህ አለ፦ “እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አለ፦ እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ፤ |
ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝቦቹን ለማጥፋት ዐቅዶ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የመረጠው ሙሴ በመካከል በመቆም፥ እንዳያጠፋቸውና ቊጣውንም እንዲመልስ እግዚአብሔርን ለመነ።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ጸሎታቸውን ሰማሃቸው፤ ይቅር ባይ አምላክም ሆንክላቸው፤ ነገር ግን ስለ በደላቸው እነርሱን ከመቅጣት ቸል አላልክም።
ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “በደስታ እጸልይልሃለሁ፤ ለአንተና ለመኳንንትህ ለሕዝብህም የምጸልይበትን ሰዓት ብቻ ወስንልኝ፤ ከዚያም በኋላ ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ ርቀው በዐባይ ወንዝ ብቻ ተወስነው እንዲኖሩ አደርጋለሁ” አለው።
ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤