ነህምያ 7:60 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምርኮ የተመለሱት የቤተ መቅደስ ሠራተኞችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች ብዛት ጠቅላላ ድምር 392 ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች 392 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ሁሉና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። |
ቴልሜላሕ፥ ቴልሐርሻ፥ ከሩብ፥ አዶንና ኢሜር ተብለው ከሚጠሩት የገጠር ከተሞች የተመለሱ የደላያ፥ የጦቢያና የነቆዳ ጐሣዎች ወገኖች የሆኑት ዘሮች ድምር 642 ነበር፤ ይሁን እንጂ እነዚህ ሁሉ የእስራኤል ዘሮች መሆናቸውን ለማወቅ የሚያስችል በቂ ማስረጃ አልነበራቸውም።