La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 15:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ ግን አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን ‘ከእኔ የምታገኙትን ርዳታ ለእግዚአብሔር መባ አድርጌ አቅርቤአለሁ’ ቢላቸው፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እናንተ ግን፣ ማንም ሰው አባቱን ወይም እናቱን፣ ‘ከእኔ ማግኘት የሚገባችሁን ርዳታ ሁሉ ለእግዚአብሔር መባ እንዲሆን ሰጥቻለሁ’ ቢላቸው፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተ ግን እንዲህ ትላላችሁ ‘አባቱን ወይም እናቱን “ከእኔ የምትጠቀመው ሁሉ መባ ነው የሚል ሁሉ፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እናንተ ግን ‘አባቱን ወይም እናቱን “ከእኔ የምትጠቀምበት መባ ነው የሚል ሁሉ፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተ ግን፦ አባቱን ወይም እናቱን፦ ከእኔ የምትጠቀምበት መባ ነው የሚል ሁሉ፥

Ver Capítulo



ማቴዎስ 15:5
9 Referencias Cruzadas  

በኋላ እንዳትጸጸት ለእግዚአብሔር ከመሳልህ በፊት ተጠንቅቀህ አስብ።


እግዚአብሔር ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ በአባቱ ወይም በእናቱ ላይ የስድብ ቃል የተናገረ በሞት ይቀጣል’ ብሎ አዞአል።


‘ያ ሰው አባቱን [ወይም እናቱን] ማክበር አያስፈልገውም’ ትላላችሁ፤ ስለዚህ ወጋችሁን ለማጥበቅ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ሕግ ታፈርሳላችሁ፤


ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ ለእናንተ መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ተገቢ ነውን? እስቲ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።


ጴጥሮስና ሌሎች ሐዋርያት ግን እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ለሰው ከመታዘዝ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባናል፤